የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መልሶ መቋቋሚያ ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ፡፡

Latest News

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የትግራይ የሽብር ቡድን ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ ዘረፋና ውድመት ላደረሰበት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ግብዓቶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ድጋፉን ደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቱሉ አውሊያ ካምፓስ ድረስ ይዞ የመጣው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የልዑካን ቡድን የመጡበት ዩኒቨርሲቲ ካለው የመማር ማስተማር ግብዓቶች ቀንሶ አጠቃላይ ግምቱ 1729066/ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃያ ሺህ ስልሳ ስድስት/ ብር የሚያወጣ የተለያዩ ግብዓቶች ለዩኒቨርሲቲው መልሶ ማቋቋሚያ በስጦታ ማበርከቱን ገልፆ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከጎኑ እንደማይለይ አሳውቋል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲም ለተደረገለት የመቋቋያ ድጋፍና አጋርነት በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል፡፡ የካቲት 1 /2014 ዓ.ም,

Leave a Reply

Your email address will not be published.