የጊዜ አጠቃቀም ስርዓት ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የሰውሀብት ልማቱን በአመለካከት፣ ፣በክህሎት ና በውቀት በማበልጸግ የተሻለ ፈጻሚ የመፍጠር ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡ በዚሁ መሰረት ከግንቦት 15- 19 /9/2013 ዓ.ም በሁለት ዙር በቱሉ አውሊያ ግቢ ለሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞች የጊዜ አጠቃቀም ስርዓትና የጊዜ አስተዳደር ስርአት ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰውአገኝ አስራት ስልናውን ባስጀመሩበት ወቅት እነድደገለጹት ‹‹ ካለን ሀብት መካከል ለሰውልጆች እኩል የተሰጠን ሀብት ቢኖር ጊዜ ነው › ነገርግን በአጠቃቀም ልዩነት ጊዜያችንን እኩል ስልጠቀምበት እንታይም ፡፡የዚህ ዋናው ምክንያት ጊዜ እንድ ጊዜ ካለፈ መልሶየማይመጣ ሀብትመሆኑን ባለመገንዘብ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ስልጠና የጊዜ አጠቃቀም ባህላችንን እንድናሻሽል በር የሚከፍት ነው›› ሲሉ እሰረድተዋለል ፡፡የዩኒቨርሲቲው የሰው ሀይል አሰተዳደርና ልማት ዳይሬክተር አቶ አረጋ ሊበን በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ለሰውሀብት ልማት ቅድሚያ በመስጠት የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን እንድንሰጥ በፈጠረልን እድል መሰረት የፈጻሚውን አቅም ለማጎልበት ስልጠናዎችን እየሰጠን እንገኛለን ሲሉ ገልጸው በተሰጠው የጊዜ አሰቃቀም ስርዓት ስልጠና ማግስት የሰልጣኙን ለውጥ መከታተል ሌላ ስራ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡ሰልጣኞችም በስልጠናው ማጠቃለያ በሰጡት አስተያየት ‹‹የሚሰጡት ስልጠናዎች አቅም እንደሚፈጥሩላቸው ያለቸውን ሀሳብ ገልጸው ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.