የጥሪ ማስታወቂያ

Latest News

በ 2014 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ 1ኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፦በቅድሚያ በሃገራችን ከሚገኙ አጠቃላይ( comprehensive) ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ወደሆነው የሰላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአብሮነት ተመሳሌት ወደሆነው መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልንየምዝገባ ቀን ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ. ም መሆኑን እየገለጽን1ኛ. በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባቸሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቦታ በቱሉ አዉሊያ ካምፓስ (በዋናዉ ግቢ) ሲሆን2ኛ. በሶሻል ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ተማሪዎች በመካነሰላም ካምፓስ መሆኑን እየገለጽን፤ አዲስ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ከ 8ኛ_ 12ኛ ክፍል ያለዉን የትምህርት ማስረጃ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒ ፣ ፎቶ ግራፍ ( 3X4) ብዛት 8፣ ብርድ ልብስ፣አንሶላና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባቸኋል፡፡ ማሳሰቢያ  ዩኒቨርሲቲው ከምዝገባ ቀናት ዉጭ ቀድመው ወይም ዘግይተው ለሚመጡ ተማሪዎች አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡ በዋናው ግቢ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ተማሪዎች አካባቢው ቀዝቃዛ ስለሆነ ለብርድ የሚሆኑ አልባሳትን ይዛችሁ እንደትመጡ ይመከራል፡፡ በ 2013 ዓ.ም 1ኛ ሰሚስተር ተመዝግባችሁ በግል ችግር ምክንያት ዊዝድራዋል ሞልታችሁ የሄዳችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን። የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published.