ለፖሊስ አባላት ስልጠና ተሰጠ።

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር በዞኑ ስር ለሚገኙ የመምሪያው ዋና እና ንዑስ የስራ ክፍል ሃላፊዎች ና ወረዳ የፖሊስ ዋና እና ንዑስ የስራ ክፍል ሓላፊና አባላት የተሳተፍባት ስልጠና ከግንቦት 14-15 /2013 ዓ.ም ለ2 ተከታታይ ቀናት በማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ፤የሰው መግደል ወንጀልን መከላከል ፤ የፖሊስ ስነ ምግባር ና ስብዕና ግንባታና የስብዓዊ መብት ና ያለ እድሜ ጋብቻ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስልጠናነው፡፡የደቡብ ወሎ ዞን የሰላምና ህዝብ ደህንነት መምሪያ ም/ ሃላፊ ኮሎኔል ጌታዊ ዘገየ በስልጠናው የመክፈቻ ንግግራችው እንደገለጹት <<ፖሊስ የህዝብን ደህንነት የመጠበቅ ሀላፊነቱ ከፍ ያለ በመሆኑ ወንጀልን የመከላከል ስልትን በብቃት ለመወጣት ያስችለን ዘንድ ዩኒቨርሲቲው የፈጠረልን አጋጣሚ ጥሩ ነው ›› ሲሉ ለሰልጣኞች አስገንዚበዋል ፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ.ር ካሳሁን አህመድ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር የጀመረውን አጋርነት አጠናክረንበመስቀጠል የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት እንድከበር እንድሁም ወንጀል ጠል የሆነ ማህበረሰብ በመፍጠር ልማትን መፋጠን እንድቻል ስልጣኞች ካላቸው እውቀት ላይ በመጨመር የፖሊሲ ሙያን የተላበሰ ሀገሩንና ህዝቡን የሚውድ አባል እንድኖር ለማስቻል የታሰበ ነው ሲሉ ለሰልጣኖች ግንዛቤ ፈጥረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.