መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ ዩኒቨርሲቲ አቅም ማሻሻያ የተመደቡ ተማሪዎችን ውጤታማ ለማዲረግ እየሰራ ነው፡፡

Info Latest News

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተለያዩ ሪፎረሞችን አውጥቶ እየሰራ ይገኛል ፡፡ የዚሁ አካል የሆነው የ12ኛክፍልን ሀገር አቀፍ ፈተና ኩረጃን በመከላከል በሚያስችችል በጠበቀ ድሲፕሊን የ2014ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በዩኒቨርቲዎች እንድፈተኑ ተደርጓል ፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎችን በቅድመ ዩኒቨርሲቲ የ4 ወር ያቅም ማሻሻያ እንድወስዱ በተደረገው መሰረት በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አቅም ማሻሻያ ለሚውስዱ ተማሪዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡በዙሪያው ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ9-12ኛ ክፍል ያሉ መማሪያ መጽሃፍትን በማሰባሰብና በየትምህርት አይነቱ ከ9-12ኛክፍል የሚያገለግሉ መረጃ መጽሀፍትን በመግዛት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡የ24 ሰዓት የቤተ-መፅሀፍት አገልግሎት መስጠት ከ9-12ኛ ክፍል በየትምህርት አይነቱ አጋዥ መፅሀፍትን በቤተመጽሃፍት በማስቀመጥ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጣለበትን አደራ እየተወጣ ይገኛል ፡፡ለዚህ ተግባር የተመደቡ የግቢው መምህራን የተፈቀደላቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም በልዩ ሁኔታ ለተምህርት ጥራት የድርሻቸውን እየተወጡ ያገኛሉ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.