መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስናከፍተኛ ትም/ት የፖሊሲና ስትራቴጂክ ዕቅድ ፕሮግራሞችና የአስር ዓመት ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች ላይ ስልጠና ሰጠ ፡፡

Latest News

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ‹‹የጠራ የሳይንስና ከፍተኛ ትም/የፖሊሲና ስትራቴጅ ዕቅድ ፕሮግራሞችና ቁልፍ የውጤት ግንዛቤና ትግባራ ለኢትዮጵያ እድገት፣ ልማትና ብልጽና›› በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ስልጠና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ስራተኞች ና መምህራን በተገኙበት በሁለቱም ጊቢዎቹ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ይዘቶች ፡-ብሄራዊ የሳይንስ ፖሊሲና ስትራቴጂ፤የከፍተኛ ትምህርት ንዑስ ዘርፍ ፖሊሲና ስትራቴጂ፤የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአስር ዓመት ልማት ዕቅድ፤የሳይንስ ትምህርት ዘርፍ የአስር ዓመት ልማት ዕቅድ፤የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ቁልፍ አመላካቾች የሚሉ ናቸው፡፡የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምሬ ዘውደ በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ወቅት እንደገለጹት ‹‹ይህ ስልጠና የሃገራችንን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የምናከናውናቸውን የአጭር እና የረጅም ጊዜ የፖሊሲ ና ስትራቴጅ ትግበራ የጠራ ግንዛቤ በመያዝ ተግባሮችን ለይተንና አውቀን በክህሎት፣በዕውቀትና በአመለካከት የተሻለ ፈፃሚ በመፍጠር መስራት እንድንችል በር ይከፍታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሹመት አሰፋ አክለው እንደገለፁት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው ተልዕኮ መሰረት የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች በተዋረድ ለሚገኘው የተቋሙ መምህራንና ፣የአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውን በወሰዱበት ወቅት ሰፋ ያሉ ጥያቄዎችና አስትያየቶች የቀረቡ በመሆኑ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በዩኒቨርሲቲው ሊከናወኑና ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጠቃሚ ሃሳቦች ቀርበው ሰፊ ምክክር ተደርጎባቸው ተጠናቋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ሰልጣኞችም በበኩላቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፖሊሲና ስትራቴጅ ዕቅድ ፕሮግራሞችና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች የተሸለ ግንዛቤ እንደተፈጠረላቸው አስተያየት በመስጠት ተጠናቋ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.