“በሀገር ግምባታ የምሁራን ሚና” በሚል ርዕስ ላይ ለ4 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የምሁራን የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።

Info Latest News

ታህሳስ 25/2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያው ዙር በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ካውንስል አባላት እና በሁለተኛው ዙር በአጠቃላይ መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ከታህሳስ 22-25/2015 ዓ.ም ለ4 ተከታታይ ቀናት ያክል ሲካሄድ የቆየው የምሁራን የውይይት መድረክ ተጠናቋል። የውይይቱ አንኳር ነጥቦችም በባለፉት አራት አመታት የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች፣ ቀጣይ የርብርብ መስክና የምሁራን ሚና ላይ ትኩረት ያደረጉ ነበሩ። በውይይቱም ምሁራኑ አሉ የሚሏቸውን ፈተናዎች፣ተግዳሮቶችንና ተስፋዎች በጥያቄና አስተያየት መልክ በጥልቀት በመወያየት በቀጣይም ለሀገር ግንባታው ጠቃሚ የሚሏቸውን ነጥቦች በዝርዝር አንስተዋል፡፡ በውይይቱ የተነሱ አጅግ ጠንካራ፣ ምሁራዊ እና ለሃገረመንግስት ግንባታው ሂደት ጠቃሚ ሃሳቦችም ከመድረክ ንግግር ባለፈ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ግብአት እንድሆን ምሁራኑ አሳስበዋል። ምሁራኑ ያቀረቧቸው ጥያቄዎችን ና አስተያየቶችን ባለፉት አራት አመታት ካጋጠሙ የውስጥና የውጭ ችግሮች፣ ከአለም አቀፍ የኢኮኖሚና የሀይል የበላይነት፣በየሴክተሩ የሚስተዋሉ የፖለቲካ አዝማሚያ ፣ከሀገራዊ አቅም ፣ተስፋና ፈተና፣ ከተመዘገቡ ስኬቶች፣ ከዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ችግሮች፣ የምሁራን ቀጣይ የላቀ ተሳትፎ ከሚጠይቁ ጉዳዮች አንፃር የተነሱ እንድሁም ሌሎች የተነሱ ጉዳዮች ላይ ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የቀረቡ ሃሳቦችም በሪፖርት መልክ ለሚመለከተው አካል እንደሚቀርብ ሰብሳቢዎቹ ገልፀዋል።

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.