በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሁለቱም ካምፓሶች ለሚገኙ የሂሳብ ሰራተኞችየአይቤክስ ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  15 ለሚሆኑ የሂሳብ ሰራተኞች ለ5 ተከታታይ ቀናት አይቤክስ የተባለ ዘመናዊ  የሂሳብ አመዘጋገብ ስርዓት  ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

በገንዘብና ኢኮኖሚ  ልማት ሚኒስቴር  የአይቤክስ ባለሙያ የሆኑት  አቶ  ወንድሰን  አስፋው  የስልጠናው አላማ የፋይናንስ ስርዓቱን የተቀላጠፈ ለማድረግና ዘመናዊ የሂሳብ አመዘጋገብ ስርዓትን ለመከተል  መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

የስልጠናው ትኩረትም የወጭ አመዘጋገ ስርዓትን ቀልጠፋ የማድረግ/expediture/፣የበጀት ቁጥጥር ስርዓቱን የማሻሻል /budget control/ ና የበጀት ማስተካከል /budget adjustment/  ተግባራት ላይ መሆኑን ጨምረው  አስረድተዋል፡፡

አቶ ወንድወሰን አስፋው  ባስተላለፉት መልዕክትም በቀጣይ ከዚህ የተሻሉ ዘመናዊ አሰራሮች እየመጡ ስለሆነ እራስን ለቴክኖሎጅ  ክፍት በማድረግ አዳድስ አሰራሮችን በመከተል እና   በማሻሻል   ለዘመኑ የሚመጥን ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ  አስገንዝበዋል፡፡

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  የውስጥ ኦድት የቡድን መሪ የሆኑትና ስልጠናውን የተከታተሉት  አቶ ክብረት ተፈራ እንደተናገሩት ስልጠናው ዘመናዊ  የሂሳብ አመዘጋገብ ስርዓትን በመከተል ጊዜን ለመቆጠብና ስህተትን ለመቀነስ  እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

                  መጋቢት 10/2011 i/aF=�™w

Leave a Reply

Your email address will not be published.