በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ እና በደቡብ ወሎ ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ትብብር ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ዞን ቴ/ሙ/ኢ/ልማት መምሪያ ጋር በመተባበር በመምሪው በስሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች፣የወረዳ ቴ/ሙ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት ሃላፊዎች ፣አስተባባሪዎች እና የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ ድኖችን ያሳተፈ ከየካቲት 25-26/2013 ዓ.ም ለ2 ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡የደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክ ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ም/ሃላፊ አቶ ታረኝ ተፈራ እንደገለጹት ስልጠናው መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በፈጠረልን ምቹ ሁኔታ በዞናችን ስር ለሚገኙ አስፈጻሚ አካላትን አቅም በማሳደግ ኢንተርፕራይዞችንና ስራ ፈላጊ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስልጠና እንደሚሆን ተናግረው ትኩረት ያደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን 4ቱ የድጋፍ ማዕቀፍ፣የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር አተገባበር፣ የተዘዋዋሪ ብድር፣የመስሪያና መሸጫ ብድር ዙሪያ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እንደሆነ ገልጸዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው የጥናት ምርምርና ማህበርሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ በበኩላቸው እንደገለጹት የደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክ ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ጋር በፈጠርነው የአጋርነት የስምምነት ሰነድ መሰረት ‹‹የድርሻ ድርሻችንን በመወጣት የኢንተርፕራይዙንና የስራ ፈላጊውን ማህበረሰብ አቅም እናሳድግ ›› በሚል አስተሳሰብ የአስፈጻሚው አካልን ክህሎት በማሳደግ በየደረጃው ያሉ ኢንተርፕራይዞችና ስራ ፈላጊ ወጣቶችን አቅም እንዲያሳድጉ የተሰጠ ስልጠና እንደሆነ ገልጸው አጋርነታችንን የበለጠ በማጠናከር ስራ ፈላጊ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡website- https://mkau.edu.et/fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.Universitytwitter- https://twitter.com/mekdela_ambaLinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mauYouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን! የካቲት 26/2013

Leave a Reply

Your email address will not be published.