በባህል፣ቅርስና ሀገር በቀል እውቀቶች ላይ ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቱሉ አውልያ ካምፓስ በባህል፣ቅርስና ሀገር በቀል እውቀቶች ጥናት ማስተባበሪያ ከስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህራን ጋር በመተባበር ከ16-17/2013 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለ2ኛ እና 3ኛ አመት ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ባህልና የባህል እሴቶች ፋይዳ፣ስነ-ምግባርና ግብረ-ገብነት እንድሁም የሀገር ፍቅር የሚሉት ርዕሰ ጉዳዮችም ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻዎል እንዳሉት ኢትዮጵያ ሀገራችን የበርካታ ባህል፣ቅርስና እሴቶች ባለቤት በመሆኗ እነዚህን ሀብቶች በአግባቡ በማወቅ፣በሀሳብ ብዝሀነት በማመን፣መጥፎ የሆኑ መጤባህሎችን በማሰወገድ፣የሰለጠነ የውይይት ባህልን በማዳበር እና ዜግነታችንን በማክበር በጋራ ሀገራችንን መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ባህል፣ቅርስና ሀገር በቀል እውቀቶች ጥናት አስተባባሪና መምህር የሆኑት አቶ አብረሃም በቀለ በበኩላቸው እንደገለፁት የስልጠናው አላማኢትዮጵያዊያን አንድነታችንን የሚያጠናክሩ ውብና ድንቅ ባህሎች ያሉን በመሆኑ እነሱን አጉልቶ በማሳየት ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ከሚያገኙት እውቀትና ክህሎት በተጨማሪ በግብረ-ገብነትና አመለካከት ላይ ለውጥ ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡ስልጠናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከሀድያ የመጣው ተማሪ ደገፉ ጌታቸው እንደተናገረው ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድ የሚገኙበት ትንሿ ኢትዮጵያ በመሆኗ አንዱ የሌላውን ባህልና እሴት መረዳትና ማክበር እንዳለበት እንድሁም በስነምግባር የታነፀ ምክንያታዊ ወጣት ከተፈጠረ ለሰላም ግንባታና ለሀገር እድገት ወሳኝ መሆኑን ተረድቻለሁ ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.