በ2015 በአድስ ወደ ስራ የሚገቡ የጥናት ትልሞች ጸደቁ፡፡

Research news

መጋቢት4/2015 ዓም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ምርምር ፣ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ካውንስል አባላትና የምርምር ስነምግባር ኮሚቴ አባላት በጋራ በትምህርት ክፍል እና በኮሌጅ ደረጃ እንድሁም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በሚመለከታቸው አካላት ተገምግመው በቀረቡ የጥናትና ምርምር 38 ፣ በማህበረሰብ አገልግሎት 18 እና በቴክኖሎጅ ሽግግር 6 በጥቅሉ 62 የጥናት ትልሞች የቀረቡ ሲሆን ኮሚቴው ሰፊ ውይይት በማድረግ ለአካባቢው ማህበረሰብ አዋጭ ና ችግር ፈች ናቸው ያላቸውን በምርምር 19፣ በማህበረሰብ አገልግሎት 7፣ በቴክኖሎጅ ሽግግር 3 በድምሩ 29 የጥናት ትልሞች በበጀት አመቱ በአድስ እንድሰሩ ፀድቋል ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤትተወካይ ኃላፊ አገኝሺበሺ (ዶ/ር) እንደገለጹት እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጠው ያላለቁ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች እንድቀጥሉ የተወሰነ ሲሆን በአድስ የሚሰሩት ካላቸው ዘላቂ ጠቀሜታ ፣አዋጭነትና ችግር ፈቺነት ታይቶ በአድስ እንድሰሩ ካውንስሉ ማፅደቁን ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.