ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በመቅዳላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ።

Latest News

መጋቢት 7/2015 ዓ.ም የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ለ47ኛ ጊዜ፣ በመቅዳላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል መጋቢት 6/2015 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል።የዩኒቨርሲቲው የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ አቶ አበበ ፀጋው በዓሉ በዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር መቆየቱን ጠቅሰው በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ለተከታታይ 5 አመታት ሲከበር መቆየቱን በማስታወስ ዳይሬክቶሬቱ በበጀት አመቱ በሴቶች ዙሪያ ያከናወናቸውን ተግባራት እንድሁም አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ ዳራ ላይ ገለፃ አድርገዋል። የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ሰራተኞች ፎረም ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰብለወርቅ አበበ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው የሴቶች ፎረም በ2015 ዓ.ም ያከናወናቸውን ተግባራት፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ወደ ፊት በትኩረት መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን እለቱን የሚዘክሩ የስነፅሁፍ ስራዎችም ቀርበዋል፡፡በመጨረሻም ከታዳሚው ጋር ውይይት ከተካሄደ በኋላ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.