የመቅደላ አምባ ዩነ ቨርሲቲ የ2014 እቅድ አፈጻጸምና  የ2015 እቅድ  ኦረንቴሽን አካሄደ፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲው የ2014 እቅድ አፈጻጸምና የ2015 እቅድ  ኦረንቴሽን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ዳይሬክተሮች፣ ድኖችና የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት  ሀምሌ 20/2014 ዓ.ም አካሂዷል፡

በመጀመሪያም በ2014 ዓ.ም በሁለቱም ካምፓስ የሁሉም የስራ ክፍሎች  ክንውኖችና የ2015 ዓ.ም  እቅድ ኦረንቴሽን በዩኒቨርሲቲው የእቅድ ዝግጅት አማካይነት ቀርቦ ግምገማ የተካሄደበት ሲሆን የግምገማው አላማም ጥንካሬያችንን ለማስቀጠል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2014  ዓ.ም ወረራ የተፈፀመበትና ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት  አመት በመሆኑ  ፈታኝ ጊዜ ቢሆንም በአመራሩና በመላው ሰራተኛ ከፍተኛ  ጥረት  የተደረገ በመሆኑ ትልልቅ ፕሮጀክቶች የተጀመሩበትና የዩኒቨርሲቲውን ሁለንተናዊ አቅም ለማደራጀት መልካም ስራ የተሰራበት አመት መሆኑም ተገምግሟል፡፡

በሌላ በኩል ሀላፊነትን በአግባቡ ያለመወጣትና  አንዳንድ  አሉታዊ  አዝማሚያዎች  የታዩም በመሆኑ  እነዚህ ላይ እርምት በማድረግ  የዩኒቨርሲቲውን  ሃገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት እንደሚሰራም በውይይቱ ወቅት ተገልጿል ፡፡   

በመጨረሻም  የዩኒቨርሲተው ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ታምሬ ዘውደ  ባስተላለፉት መልዕከት  ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ ተልዕኮን የተሸከመ ትልቅ ተቋም በመሆኑ በመማር ማስተማሩ ብቁ ምሩቃንን ለማፍራት፣በምርምሩ  ችግር ፈቺ የሆኑና ስር ነቀል ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት እንድሁም የተጀማመሩ  ትልልቅ ፕሮጀክቶችንና ማህበረሰብ  አቀፍ ስራዎችን በማጠናከር  ውጤታማ ስራ ለመስራት  ሁሉም በየደረጃው በሀላፊነት ስሜት  መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

                                                      ሀምሌ 21/2014 ዓ.ም

Exif_JPEG_420
Exif_JPEG_420
Exif_JPEG_420
Exif_JPEG_420

Leave a Reply

Your email address will not be published.