የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መሰረታዊ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ፡፡

Latest News

ህዳር 7/2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሀላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ሰኔ 11/10/2011ዓ.ም ህጋዊ እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ ሲሆን የማህበሩ ዋና አላማም የፍጆታ ምርቶችና አገልግሎቶች ለአባሉ እንድቀርብ ማመቻቸት መሆኑ በጉባኤው ወቅት ተገልጸዋል፡፡ጉባኤው አመታዊ የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ላይ መወያየት፣የ2014 ዓ.ም ኦድት ሪፖርት ማፅደቅና የ2015 ዓ.ም እቅድ ማፅደቅ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ማህበሩ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን በገበያው ችግር ምክንያት ከካፌ አገልግሎቱ ውጭ ሌሎች እህልና ሸቀጣሸቀጥ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የማቅረብ ውስንነት፣የመስሪያና የመሸጫ ቦታ እንዲሁም የካፒታል እጥረት የሚሉት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ተብለው የተለዩ ሲሆን ይህንንም ችግር ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካለት ጋር በመነጋር ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ አረጋ ሊበን አሰገንዝበዋል፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published.