የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም ግንባታ ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  አመራሮች፣መምህራን፣ሰራተኞችና ተማሪዎች  የተሳተፉበት በብዝሀነት፣በመቻቻልና  በሰላም  ግንባታ ዙሪያ ከቀን 23-24/09/2011 የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

የተማሪዎች  አገልግሎት ዳይሬክተር  የሆኑትና በጉዳዩ ላይ  ፅሁፍ ያቀረቡት አቶ እያሱ ጉግሳ  መቻቻል  እንደ ኢትዮጵያ  ላለች የብዘሀነት ሀገር  ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ  ብዘሀነትን ማክበር፣መቀበልና ማድነቅ እንድሁም በልዩነት ውስጥ ስምምነት  መፍጠር መቻል  አለብን  ብለዋል፡፡

 በዩኒቨርሲቲው  የሲቪክስ  መምህር ና ሌላው  በጉዳዩ ላይ  ፅሁፍ  ያቀረቡት አቶ ኢሳ መሀመድ  ሰላም  የምንጊዜም ንጉስ  ቃል ና ውድ  በመሆኑ ከራሳችን በመጀመር  ልንጠብቀውና ልንከባከበው ይገባል ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው መንግስት  መሰረታዊ የሆነውን  የግጭት መንስኤ  ለምን ማጣራት አልቻለም ህገመንግስት ማሻሻል ለምን አልተቻለም  የተለመደ እኛ እናቅላችኋለን ስብሰባና ለማሳመን መሞከር ለምን አይቀርም የሚሉና ሌሎች በርካታ ጥያቆችን ና አስያየቶችን አንስተዋል፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻወል  በበኩላቸው ማጠቃለያ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በሀገራችን  በርካታ ችግሮች እንዳሉ  ገልፀው  ነገር ግን  ሰላም የማስጠበቅ ጉዳይ ቅድያ ሊሰጠው  እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

ግንቦት  2011 cla3���U

Leave a Reply

Your email address will not be published.