የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በወቅታዊ ሰላማዊ መማር ማስተማር ጉዳይ ላይ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  ተፈጥሮ በነበረው መጠነኛ ግጭትንና ያለመረጋጋትን ምክኒያት በማድረግ ለችግሩ  እልባት ለመስጠትና  ሰላማዊ መማር ማስተማሩን በተገቢው መንገድ ለማስቀጠል ያለመ በሁለቱም ካምፓሶች  የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አመራሮች፣የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች፣ተማሪዎች፣የሃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ሃይሎች  በተገኙበት  ውይይት አካሂዷል፡፡

ውይይቱን የመሩት የዩኒቨርሲው የቦርድ ሰብሳቢ እና የፌዴሪ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት አቶ ገለታ ስዩም እንደተናገሩት  በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከሚመለከተው አካላት ሁሉ ጋር  ተወያይቶ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ያስቀመጠው የመፍትሄ  አቅጣጫ ሶስት አማራጮች ሲሆኑ አንደኛው  ተግሳፅን ጨምሮ በማስጠንቀቂያ የመሳሰሉት  የሚታለፍበት ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ በወንጀል የሚጠረጠሩ አካላት በህጋዊ አግባብ እርምጃ እንድወሰድባቸው ማድረግና ሶስተኛው የሀገር ሀብትና የሰው ህይወት መጥፋት የሚቀጥል  ከሆነ የመጨረሻው አማራጭ ዩኒቨርሲቲዎችን መዝጋት ይሆናል ብለዋል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ም/ሰብሳቢ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት  በህብረተሰቡ ስስ ብልት  በኩል  እየመጣ እስትራቴጅ ተኝቶ እየነደፈ  ህዝብ የሚያዋጋና ሀገር እንዳትረጋጋ የሚያደርግ አካል ስላለ ለየት ያሉ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል  ለህግ ተባባሪነታችሁን እንድትቀጥሉ እኛ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ቆርጠን የተነሳን ሲሆን  ወንጀለኞችንም መንጥረን እናወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ እዳሉትም  በዩኒቨርሲቲው በኩል የምግብ የውሃ ሌሎች  አስተዳደራዊ ችግር  እዳይኖር እየሰራን ሲሆን ከኛ በተቃራኒም እንደት እረብሽ ማስነሳት እንዳለባቸው የሚመክሩ አካላት ስላሉ ከስከዛሬው በበለጠ ሁኔታ በሰላማችን ላይ በየጊዜው እየተገናኘን መምከርና ሴራቸውን ማክሸፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ከዩኒቨርሲቲው ጎን በመቆም ምንም አይነት ቁሳዊም ሆነ የህይወት አደጋ ሳይደርስ ችግሩ እድከሽፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡

 በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት ግጭቱ በኦሮሞና አማራ ተማሪዎች  መካከል  ሳይሆን የስልጣን ሽኩቻ የሚያካሂዱ አካላት መካከል በመሆኑ እኛ ተማሪዎች  ህይወታችንን ገብረን የነሱ አላማ ማስፈፀሚያ መሆን  የለብንም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከህበረተሰቡ የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎችም የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች በምክርም በማስተማርም ሁሉምን በእኩልነት እንደልጆቻቸው በማየት የአካባቢያቸውንና የሀገራቸውን ሰላም  ለመጠበቅ  እንደሚሰሩና ህገወጦችን በንቃት በመከታተል  ለህግ እንደሚያቀርቡ  ተናግረዋል፡፡

                        ህዳር 15/2012

Leave a Reply

Your email address will not be published.