የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በጃማ ወረዳ ለሚገኙ ሞደል አርሶ አደሮች የመስክ ድጋፍ አደረገ፡፡

Latest News Research news

ዩኒቨርሲቲው 2011 ዓ.ም ክረምት ላይ በክላስተር ለታቀፉ ሞደል አርሶ አደሮች አሰራጭቶ የነበረውን ምርጥ የስንደ ዝርያ  አሁን ያለበትን ሁኔታ ቦታው ላይ በመገኘት የመስክ ላይ ድጋፍ አካሂዷል፡፡

በጃማ ወረዳ 08 ቀበሌ ነዋሪና ዳንፌ የተባለ ምርጥ የስደ ዝርያ ዩኒቨርሲቲው ካሰራጨላቸው አንዱ የሆኑት  አርሶ አደር ካሱ አባተ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸውን የግብአትና የሙያ ድጋፍ በመጠቀም በትክክል በመዝራታቸውና በማረማቸው ጥሩ ሰብል ለማየት እንደበቁ ና ያለብንን የማዳበሪያ እጥረት ቢቀረፍላቸው የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

አቶ ነጉ አሰፋ በጃማ ወረዳ 08 ቀበሌ የግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ ዩኒቨርሲቲው እያደረገ  ያለውን ድጋፍ  አመስግነው  ዩኒቨርሲቲው የጀመረውንም ድጋፍ  አጠናክሮ ከቀጠለ የአርሶ አደሩ  የኑሮ ደረጃ  ይሻሻላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትና የመስክ ድጋፍ የደረጉት አቶ ካሰሁን እንዳሉት አንዳንድ አርሶ አደሮች  የተሰጣቸውን ዘር ባግባቡ በክላስተር ያለመዝራትና አረም  በወቅቱ ያለማረም ችግሮች ማስተዋላቸውንና በተረፈ ባዩት ሰብል መርካታቸውን ገልጸዋል፡፡

                                             መስከረም 27/2012 �7�t#B

Leave a Reply

Your email address will not be published.