የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት አባላት መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ፣ለአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ የአንድ ወር ደመወዛቸውን በመስጠት ከጎን መሰለፋቸውን አረጋገጡ፡፡

Latest News

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በቀን 17/12/2013 ዓ.ም ባደረገው ውይይት የሃገርን ክብር ለመጠበቅ ቀን ከሌሊት በዱር በገደሉ የሃገር ከሃዲዎችን በመተናነቅ ውድ ህይወታቸውን አሳልፈው ለሰጡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ለአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖድጋፍ የሚውል በ 11 ወር የሚከፈል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ብር 3,596,179(ሶስት ሚሊየን አምስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ) ብር በላይ ድጋፍ ለማድረግ ባደረጉት ስብሰባ ወስነዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምሬ ዘውዴ እንዳሳሰቡት የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ለሃገራችን ክብር በውስጥም ይሁን በውጭ ጥላት ለመመከት እየተፋለሙ ያሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖዎች በገንዘብ ብቻ ሳይሆን ደም በመለገስ፣ የዘማች ቤተሰብ አረም በማረም ፣ለተጠባባቂ ሃይል እራስን በማብቃት መሰለፍ አለብን ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የወር ደመወዛቸውን ከመስጠታቸው በተጨማሪ አካባቢያቸውን በመጠበቅ ደም በመለገስ እና የዘማች ቤተሰብን አረም በማረም እንደሚሳተፉ ደጋፋቸውን አሳይተዋል፡፡
18/12/2014 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.