የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የ2014 ዓ.ም የኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት እና የተወሰዱ መፍትሄዎችን በማስቀመጥ የአንደኛ ሩብ የስራ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡በጽ/ቤቱ ውስጥ ያሉ ኮሌጆችና ዳይሬክቶሬቶች የሩብ አመቱን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሩብ አመቱ የተከናወኑ ጅምር ስራዎች ጥሩ አፈፃፀም እንደነበራቸው ተግምግሟል፡ በክፍተት ከታዩት መካከል የሚታየው የግዥ መጓተት፣ የመብራትና የኢንተርኔት መቆራረጥ እንድሁም ከመረጃ አያያዝ አንፃር የሚታዩ ክፍተቶች መኖር የሚሉት በዋናነት ያጋጠሙ ችግሮች ተብለው የተነሱ ናቸው፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፐሬዝደንት ዶክተር ካሳ ሻወል እንዳሳሰቡት በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሰሩት ጉዳዮች መካከል የመረጃ ወቅታዊነትና አግባበነትን ማሻሻል፣ተዋረዳዊ የስራ ግንኙነትን ማጠናከር ፣ስራን በግብር መልስና ቼክሊስት መምራት፣ የጊዜ አጠቃቀም ባህልን ማሻሻል እንድሁም ልዩ ትኩረት የሚሹ አካለትን በእቅድ አካቶ በመስራት እቅዳችንን ማሳካት አለብን ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

መስከረም 25/2014 ዓ.ም

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.