የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ አመት ተማሪዎች ሞደል ፈተናቸውን በኦላይን ወሰዱ።

Latest News

ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ሪፎርም ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከእነዚህም ሪፎርሞች መካከል አንዱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውሰድ ነው፡፡ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ካሳ ሻውል(ዶ/ር) እንዳስረዱት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ይህን የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ስኬታማ ለማድረግ በርካታ የቅድመዝግጅት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ከ2015 ዓ.ም ጥቅምት ወር ጀምሮ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን  እስከ ትምህርት ክፍል ድረስ የማደራጀት፣ ካሌንደር የማዘጋጀት፣ በሁሉም ኮርሶች ቲቶሪያል የመስጠት፣ ለመምህራንና ተማሪዎች ስልጠና እና ኦሬንቴሽን የመስጠት፣ ሞዴል ፈተናዎችን  በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰጠው ማዕቀፍ የማውጣት ስራዎች መከናወናቸውን  የካሳ ሻውል (ዶ/ር) ገለፃ ያስረዳል፡፡ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በ22/07/2015 ዓ.ም የተጀመረው የመውጫ ኦንላይን ሞዴል ፈተና ዋና አላማው ተማሪዎች ከወዲሁ ቴክኖሎጂውን እንዲለማመዱ፣ ቅድመ ዝግጅታቸውን ፈትሸው በቀሪ ጊዜያት ክፍተታቸውን እንዲሞሉ እና ዩኒቨርሲቲውም ከሞዴል ፈተናው ውጤት ትንተና በመነሳት ተማሪዎቹን ለማገዝ ሊሰሩ የሚገባቸውን ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሆነ ከገለፃው ለመረዳት ተችሏል፡፡ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታሪኩ በገለፃው ወቅት ጨምረው እንዳስረዱት ለሞዴል ፈተናው አገልግሎት የሚውል ቀላልና ሁሉም አይነት  ተማሪዎች ሊጠቀሙት የሚችል ሶፍትዌር ተዘጋጅቷል፡፡ በሶፍት ዌር አጠቃቀሙ ላይም ለመመህራንና ተማሪዎች ስልጠና እና ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፡፡ በፈተናው ወቅት ያነጋገርነው የ4ኛ አመት ተመራቂ የኮምፒውተር ትምህርተ ክፍል ተማሪ የሆነው ጥላሁን ጥጋቡ እንደሰጠው ሀሳብ ተማሪዎችን ለማገዝና ለማብቃት የሚደረጉት ጥረቶች አበረታች እንደሆኑ ገልፆ መውጫ ፈተናውን በውጤታማነት ለመቋጨት እኛ ተማሪዎች የምናባክነው ጊዜ ሊኖረን አይገባም ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡   

                                          መጋቢት/2015 ዓ.ም

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃወች፦ website- https://mkau.edu.et/ fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University twitter- https://twitter.com/mekdela_amba LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA

Leave a Reply

Your email address will not be published.