የመቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ በሁለቱም ካምፓስ የሚገኙ 824 የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡

Graduation News Latest News

የመቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎቹን በ16 የትምህርት መስኮች 824 ተማሪዎችን ጥር 8/2013 ዓ.ም በዋናው ካምፓስ ቱሉ አውሊያ እና ጥር 9/2013 ዓ.ም በመካነሰላም ካምፓስ የክብር እንግዶች የጠቅላይ ሚኒስቴር የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስዳደድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ተመራቂ ተማሪዎችና የተመራቂ ወላጆች፣የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል፡፡የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባደረጉት ንግግርም ይህ ዩኒቨርሲቲ በወሎ ማዕከላዊ ቦታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ካገኛቸሁት ድግሪ በላይ ወሎ ከየት መጣህ የማይልበት በጋራ በፍቅር የሚኖርበት የበጎነት ተምሳሌት በመሆኑ የበጎነት እሴትንም ይዛችሁ እንደምትወጡ እተማመናለሁ ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስዳደድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ባስተላለፉት መልዕክትም ክልላችን አንዳንዶች ስለ አማራ ህዝብ እንደሚያስወሩት ሳይሆን እንግዳ ተቀባይ አቃፊ ህዝብ ነው፤በመሆኑም ይህንን የተሳሳተ ትርክት በማረም እውነታውን በተግባር ያያችሁትን እንድታሳውቁ ጥሪየን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሬ ዘውደም ዩኒቨርሲቲው ከጅማሮ ጀምሮ እስካሁን የነበሩበትን ተግዳሮቶችና አሁን የደረሰበትን ስኬት አስረድተው ለዚህም አስዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ጥር 10/2013 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.