የመቅዳአምባ ዩኒቨርሲቲ አንድቀን ለህዝቤ በሚል ፕሮግራም የአካባቢ ጽዳት ዘመቻ አካሄደ፡፡

Latest News Research news

የመቅዳአምባ ዩኒቨርሲቲ ̎አንድ ቀን ለህዝቤ̎ በሚል ፕሮግራም  ጥቅምት 22/2012 ዓ.ም በሁለቱም ግቢዎች  መምህራንን ፣የአስተዳደር ሰራተኖችንና  የ2ኛና 3ኛ አመት ተማሪዎችን በማስተባበር የከተማ ፅዳት ዘመቻ አድርጓል፡፡ የቱላዉሊያ ከተማ መዘጋጃ ቤት እና  የመካነሰላም የከተማ አሰተዳዳር  አመራሮችና ነዋሪዎች በዘመቻው ላይ በደማቅ ሁኔታ ተሳትፈውበታል ፡፡ የጽዳት ዘመቻው ጽዱና የተዋበ አካባቢ ለመፍጠር ፣የአካባቢውን ማህበረሰብ ለማሰተማርና ለማነቃቃት የሚያስችል አርእያነት ያለው ተግባር እንደሆነና የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ከነዋሪዎች ጋር ለማስተሳሰር ያስቻለ ነበር፡፡ የቱሉ አውሊያ ከተማ  ነዋሪዎች ለቆሻሻሻ  መድፊያ ሲኖትራክ መኪና፣ ጋሪና የቆሻሻ ማንሻ ኬሻ በመግዛት ጭምር  ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ የከተማዋ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሻማግሌዎች  ለተደረገው መልካም ተግባር በዩኒቨርሲቲው ግቢ ተገኝተው ምሰጋናቸውን አቅረበዋል ፡፡ የቱሉ አውሊያ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አምባው አባተ  እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው እንድህ አይነቱን በጎተግባር ማድረጉ አካባቢን በትብብር ማልማት እንደሚቻል ትምህርት የሚሰጥና የማህበረሰቡን ግንዛቤ የሚያሳድግ አንዱ  ማሳያ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፡፡የመካነሰላም ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ተስፋየ ዳኘ በበኩላቸው ይህ በጎተግባር የከተማችንን ውበት ከመጠበቅ ባለፈ ጤንነቱ የተጠበቀ መህበረሰብ ለመፍጠር ጥሩ ማሳያ ነው፤ በመሆኑም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ያደረገው አስተዋጾ የከተማችን ማህበረሰብ በጽዱ አካባቢ እንድኖር  በቀጣይ  ሁሉም የግሉንና የአካባቢውን ንጽህና ለመጠበቅ መነሻ ነው›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፡፡  የመካነ ሰላም  ግቢ የጥናትና ምርምር ቡድን መሪ  መ/ር አብዱረህማን አወል  የግቢያችን ማህበረሰብ የከተማውን ውበት ለመጠበቅ ያደረገው አስተዋጾ እጅግ የሚያኮራ ነው፤ ነገር ግን የመካነ ሰላም  ከተማ ኑዋሪዎች እለቱ የገበያ ቀን በመሆኑ  ሙሉ በሙሉ አለመሳተፋቸው  ለቀጣይ ለምናደርገው ተግባር አያነሳሳም ሲሉ  ለመቅዳአምባ ዩኒቨርሲቲ የኩሙኒኬሽን ጉ/ዳርሬክቶሬት ዝግጀት ክፍል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፡፡የተማሪዎች ህብረትና የተማሪ ፖሊሶች እንድሁም ተሳታፊ ተማሪዎች በሁለቱም ከተሞች ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመስራትና  ትብብራቸውን በማሳየት በሰላም ውደ ግቢያቸው ተመልሰዋለ፡፡    

                                         ጥቅምት 22/2012 y;���T

Leave a Reply

Your email address will not be published.