የወሎ በግ ዝርያ ማሻሻያ የማስጀመሪያ ዉይይት ተካሄደ::

Latest News Research news

ህዳር 28 /2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ወሎ ዞን በተመረጡ 5 አምስት ወረዳዎች የወሎ በግ ዝርያ ማሻሻያን በተመለከተ ከተመረጡ አርሶ አደሮች ጋር ዉይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡የዉይይቱ አላማም በባለ ድርሻ አካላት መካከል የጋራ የሆነ ግንዛቤ መፍጠር፤የአጋር አካላትን ትስስር ማጠናከርና የዝርያ ማሻሻያ ማስጀመር እንደሆነ የዩኒቨርሲቲዉ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ተወካይና የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት አገኝ ሽበሽ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡የአይካርዳ ተመራማሪ የሆኑትና ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት ተስፋየ ጌታቸዉ (ዶ/ር) በበኩላቸዉ የበጎችን ዝርያ ማሻሻል ሲባል ያለዉን አጥፍቶ ሳይሆን በአለዉ ላይ ምርጥ የሆነዉንና ለኢኮኖሚ እድገት አዋጭ የሆነዉን መርጦ በማዳቀል ዉጤታማ ስራ መስራት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተጀመረው የወሎ በግ ዝርያ ማሻሻል ስራ መልካም መሆኑን ገልጸው በቀጣይ የህክምና ክትትል በአቅራቢያቸው እንደሚያስፈልጋቸውና የመኖ እጥረት እንዳያጋጥም አብሮ መታሰብ ያለበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡የዩኒቨርሲቲዉ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ካሳ ሻወል (ዶ/ር) በመዝጊያ ንግግራቸዉ የወሎ አካባቢ ምርጥ ዝርያን በመጠቀም የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ ዝቅተኛ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን በጋራ በመስራት አካባቢዉን የመለወጥ ስራ እንደሚሰራ አሳውቀዋል፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦ website- https://mkau.edu.et/ fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University twitter- https://twitter.com/mekdela_amba LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.