የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በዙሪያው ላቀፋቸው ወረዳዎች ለ2ኛ ዙር የሙዝ ችግኝ አከፋፈለ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በዙሪያው ላቀፋቸው ወረዳዎች ለሚገኙ የማህበረስብ ክፍሎች በቋሚ አትክልት ተጠቃሚ በማድረግ ወደ ቋሚ የገቢ ምንጭ እንድሸጋገሩ ከደሴ ቲሹ ካልቸር ጋር በፈጠረው አጋርነት ለአካባቢው አየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ የሙዝ ዝርያ በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት የሙዝ ተክል አምራች ወረዳዎችን በድጋሜ በመለየት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ፡፡መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ እንደገለጹት በዙሪያው ለሚገኙ ቆላማ አካባቢዎች በመስኖ ሊለማ የሚችል የሙዝ ችግኝ ከደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ጋር በተዋዋልነው ያጋራ የስምምነት ውል መሰረት የሙዝ አምራች ወረዳዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን።በመሆኑም በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ በሚገኙ ቆላማ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ 15728(አስራ አምስት ሽህ ሰባት መቶ ሃያ ስምንት) የሚሆን የሙዝ ችግኝን ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ ለቦረና ወረዳ፣ለገሂዳ ወረዳ፣መቅደላ ወረዳ፣ከላላ ወረዳ፣ወረኢሉ ወረዳ፣ወግዲ ወረዳ፣አማራ ሳይንት ወረዳ እና ለጋምቦ ወረዳን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረው በቀጣይም የቡና ፣አፕል ፣ማንጎ ችግኞችን ለማሳራጭት የችግኝ ፍላጎቶችን የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሆነ አክለው ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.