(መጋቢት /2017 ዓ.ም ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት )

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በበይነ-መረብ የሚሰጡ ትምህርቶችን ወቅቱን በዋጀ ቴክኖሎጅ በማስተማር ወጪ ቆጣቢና ቀልጣፋ የሆነ የመማር ማስተማር ስራ ለማከናወን ይችል ዘንድ በ”E-Learning” አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠና ለተመረጡ መመህራን እየተሰጠ ነው ፡፡

በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአካ/ም/ቴ/ሽ/ማ/አ/ም/ል ፕረዝዳንት ስለሺ አቢ (ዶ/ር) እንደገለጹት

መምህራን ቴክኖሎጅውን ተጠቅመው በሙሉ አቅማቸው እንዲያስተምሩ ስልጠናው በቂ እውቀትንና ክህሎትን በመፍጠር በኩል በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር መምህር ደጉ አባተ በበኩላቸው ስለ ስልጠናው አስፈላጊነት በተናገሩበት ወቅት እንዳስረዱት በበይነ-መረብ ኮርሶችን መስጠት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት በመሆኑ እንደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲም የተመረጡ ኮርሶችን በበይነ- መረብና በቅይጥ ዘዴዎች ለማስተማር ስልጠናው ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል። በበይነ- መረብ ማስተማር ማሪዎች እንደገ ሀገር ተውዳዳሪ እንዲሆኑ ከማድረጉም ባሻገር ፈጣን፣ ቀልጣፋና ወጭ ቆጣቢም መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።