የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቋል ።

University News

========================================================

ሀምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም (መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ዩግንኙነት)

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከሀምሌ 3-5/2016ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቋል ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ካሳ ሻውል ፈተናው በታቀደለት መሰረት በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የፈተና አስፈፃሚ ግብረ-ሀይል አባላት፣ የፀጥታ አካላት፣ የጣቢያ ኃላፊዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኞች እንዲሁም ተጓዳኝ አገልግሎቶችን አቀላጥፈው በመስጠት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ የተቋሙ ሰራተኞች በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም በቀጣይ ጊዜ የሚሰጠውንም የተፈጥሮ ሳይንስ ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በመጀመሪያው ዙር በተደረገው የተቀናጀና የተናበበ ርብርብ መሰረት ፍፁም ሰላማዊና ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ ሁሉም የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በድጋሜ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *