በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ስርዓትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

University News

(ነሀሴ /2016 ዓ.ም ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

እንደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ካሳ ሻውል (ዶ/ር) አገላለፅ ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ስራ ላይ ማዋል የመማር ማስተማሩን ስራ ለማዘመን፣ ውጤታማ ለማድረግ እና የትምህርት ፕሮግራሞችን ተደራሽነት ለማስፋት ጊዜው የሚጠይቀው ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ፕሬዚዳንቱ እንዳብራሩት ባለፉት አመታት በዩኒቨርሲቲው ሁለቱም ግቢዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች የተሟሉላቸው አስር (10) ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች (Smart classes) ተገንብተው በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡ አያይዘውም በአዲሱ በጀት አመት አስር (10) ተጨማሪ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች በሁለቱም ግቢዎች እንደሚገነቡ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የመረጃ ግንኙነት ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት መምህር አብርሃም በለጠ እንዳስረዱት ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን (Smart classes) መገንባት የመማር ማስተማሩን ስራ ከማቅለሉና ከማዘመኑም በላይ የተማሪዎችን የዲጅታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ለማሳደግ፣ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እና ችግር ፈቺነታቸውን ለማሻሻል በእጅጉ ያግዛል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ የእነዚህ መማሪያ ክፍሎች መገንባት የርቀትና ተከታታይ ትምህርቶችን በበይነ-መረብ ለማስተማር የሚያስችሉ፣ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የሚማሩ ተማሪዎችን ትኩረት የሚጨምሩ እንዲሁም የትምህርት መረጃዎችን በፈለጉት ጊዜ ለማገኘት ምቹ የሆኑ መሰረተ ልማቶች የተሟሉላቸው ናቸው፡፡ መማሪያ ክሎቹን በተሟላ መልኩ ለመጠቀም እንዲቻል ከመረጃ ግንኙነት ባለሙያዎች በተጨማሪ እንዳስፈላጊነቱ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና እንደሚሰጥም ዳይሬክተሩ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *