የአንድ ካርድ እና የደህንነት ካሜራ ተክኖሎጂ አገልግሎት ሊጀመር መሆኑ ተገለፅ

University News

                (ነሀሴ 25/2016 ዓ.ም ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ እንደ አንድ ትልቅ አገልግሎት ሰጪ ተቋም የተማሪዎቹን፣ የመምህራኑን፣ የሰራተኞቹን፣ የውጭ ተገልጋዮቹን፣ የንብረቶቹን እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጡን ደህንነት የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፡፡

 በዚሁ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የአንድ ካርድ አገልግሎትን እና የደህንነት ካሜራዎችን መሰረተ ልማት ለመገንባት ከህዳር/2016 ዓ.ም ጀምሮ  በሁለቱም ግቢዎች ወደ ስራ የገባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የመረጃ መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) ዳይሬክተር እና መምህር አብርሃም በለጠ አገላለፅ የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ተቋማዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን በማዘመን ለመማር ማስተማሩ ስራ ሰላማዊ እና ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ በተጨማሪም የእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ስራ ላይ መዋል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ካርድ ማግኘት እንዲችሉ ከማድረጋቸውም በላይ በግቢ ውስጥ እና በአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ሁሉ ህገ ወጥ ድርጊቶች እንይከሰቱ ለመከላከል እና ሲከሰቱም  በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላሉ፡፡

የፕሮጀክቱ ተቋራጭ አስተባባሪ ኢንጅነር ካሳየ ስዩም በበኩላቸው እንደገለፁት በቱሉ አውሊያ ጊቢ ብቻ 99 የደህንነት ካሜራዎች እና 9 ባለ ሃምሳ አምስት ኢንች ቴሌቪዥኖች በመገጣጠም ላይ ሲሆኑ የ5000 ሜትር የፋይበር ኬብል  መስመር ዝርጋታም ተሰርቷል፡፡ የቴሌቪዥኖቹም ዋና ስራ 99ኙን  የደህንነት ካሜራዎች  በአንድ ጊዜ በግልፅና በተደራጀ መልኩ ለመከታተል ማስቻል እንደሁነ ጨምረው አብራርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *