የተቀናጀ ሞዴል የተፋሰስ ልማት ስራ በደንበሽ አፋፍ ጀማ እየተከናወነ ነው፡፡

Research News Uncategorized University News

(ጥቅምት /2017 ዓ.ም ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ እና በለጋምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የጋራ ትብብር እየለማ የሚገኘው የደንበሽ
አፋፍ ጀማ ሞዴል የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ፕሮጀክቱ በ2012 ዓ.ም ቢጀመርም
በሰሜኑ ጦርነት ምክኒያት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን በ2015 ዓ.ም በአዲስ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡
የፕሮጀክቱ የስምምነት ጊዜ ለአምስት አመት የሚቆይ ነው፡፡ ይህ የተቀናጀ ሞዴል የተፋሰስ ልማት 200
ሄክታር መሬት የሚሸፍን እና 578 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግም ነው፡፡
የአፋፍ ጀማ የተቀናጀ ሞደል ተፋሰስ በደን፣ በሰብል እና በእንስሳት ዝርያዎች ማሻሻል ላይ ትኩረት
ተደርጎ እየተሰራበት ሲሆን ለእነዚሁ አበይት ተግባራት ማስፈፀሚያ የሚውል 5 ሚሊዮን 600 ሺህ ብር
በጀት ተፈቅዶለት ስራ ላይ እየዋለ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ መምህርና ተመራማሪ አንዋር ሁሴን እንደተናገሩት የፕሮጀክቱ መነሻ ሀሳብ
የተራቆተውን አካባቢ እንደገና እንዲያገግም በማድረግ የተሸሻሉ የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎችን
የሚያመርት የተቀናጀ ሞደል የተፋሰስ ልማት መፍጠርና ለአካባቢው ማህበረሰብ ችግር ዘላቂ መፍትሄ
ማምጣት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የአካባቢውን አመራርና ማህበረሰብ የማወያየት፣
የአካባቢ ዝርያ ችግኞችን የማፍላትና የመትከል፣ የተሻሻሉ 10 አውራ በጎችንና 375 እንቁላል ጣይ
ዶሮዎችን ለተመረጡ አርሶ አደሮች የማሰራጨት፣12 አባለት ያሉት የተፋሰስ ልማት ኮሚቴ የማቋቋምና
ግንዛቤ የመፍጠር እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ስራዎች መከናዎናቸውን ዋና
አስተባባሪው ጨምረው ያብራሩ ሲሆን በቀጣይም በፕሮጀክቱ እቅድ መሰረት ተግባራት ተጠናክረው
ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *