በሰብል መድህን ዙሪያ ሲምፖዚየም ተካሄደ፡፡

University News


(ታህሳስ 2016 የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በሰብል መድህን ዙሪያ “Symposium on Crop insurance syytem- Enhancing Farmer Resilience through collaboration engaging stakeholders” በሚል መሪ ሀሳብ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ሲንፖዚየም አካሂዷል፡፡
የሲፖዚየሙ አላማ ስለ ሰብል መድህን ግንዛቤ በመፍጠር የአርሶ አደሩን አደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ መሆኑን በአዘጋጆቹ ተገልጿል፡፡
የሰብል መድህን ጥቅም አርሶ አደሮች በድርቅ፣በበረዶ፣በእሳት ቃጠሎ፣ በጦርነት፣ እና በሌሎች የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሰብላቸው ሲወድም በሚያካክስ መልኩ ሰብሉን መተካት፣ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን መፍጠር ፣ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እና አዳድስ ቴክኖሎጅዎችን የማላመድ እንደሆነ በሲፖዚየሙ ወቅት ተገልጿል፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ሹመት አሰፋ (ዶ/ር) ውይይቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲዎች በእውቀትና ክህሎት ላይ የሚሰሩ ተቋማት በመሆናቸው ባላድርሻ አካለትን በማገናኘት የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየር የሰብል መድህን ላይ ግልፀኝነት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ድን የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር አማረ ግርማ በበኩላቸው ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር ግብርና የሀገራችን ዋና የኢኮኖሚ ዘርፍ እና በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የጋራ የባለ ድርሻ አካለት የጋራ መድረክ በማካሄድ ዘርፉን ለመደገፍ ሲፖዚየም ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡
ለወቅታዊ አና ታማኝ መረዎጃች
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA
ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *