በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡

University News

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡

****************************************************************

(ህዳር21/2016ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ ሙስና ቀን ‹‹ ሙስና ጥላታችን ነው ፤በህብረት እንታገለው>> በሚል መሪ ቃል ከባለደርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት በማድረግ አክብሯል፡፡

የውይይቱን መድረክ የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ሰውአገኝ አስራት (ዶክተር) በአስተላለፉት መልእክት ‹‹ ሙስና ጉቦ መቀበል ብቻ ሳይሆን የመንግስት ሀላፊነትን ላልተገባ ጥቅም ማዋል ፤መደለያ መቀበል ፣የአሰራር ስርአትን መጣስ ፣ ማጭበርበር ፣ በዝምድና መስራት እና የመንግስት የስራ ሰዓትን ማባከን መገለጫዎቹ ናቸው ብለዋል ፡፡ ለዚህም መነሻው አላግባብና በአቋራጭ መበልጸግን መፈለግ ነው ሲሉ አክለው ተናግረዋል ፡፡

ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጽሁፍ መምህር በላቸው ፈንታው ‹‹የሙስና ምንነትና የሚያስከትለው ጉዳት በሚል ርዕስ አቅርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡

በውይይቱም የሙስና ምንነት ፤ መንስኤዎችና መገለጫዎቹ፤ ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት እንድሁም ሙስናን በጋራ በመከላከል በኩል የባለ ደርሻ አካላት ሚና ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ በማቅረብ ለተሳታፊዎች ግንዛቤ ተፈጥሯል ፡፡

በተሳታፊዎች ጥያቄዎች ተነስተው በቂ ማብራሪያና የጋራ ግንዛቤ እንድያዙ ተደርጎበታል ፡፡

በማጠቃለያውም የዩኒቨርሲቲው ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፎዚያ ክብረት ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ ሙስና የሁሉም ዜጋ ጥላትና ኢኮኖሚን በማዛባት ለኑሮ ውድነት የሚያጋልጥ በመሆኑ በጋራ ልንዋጋውና ልንታገለው ይገባል ፡፡ስለሆነም የሙስና ወንጀልን ማጋለጥ ና መታገል የዜግነት ግደታ መሆኑን መታወቅ አለበት›› ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *