ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረዉ ዓለም አቀፉ የአብሮነት ቀን “ብዝነትን መኖር!” በሚል መሪ ሐሳብ ከታኅሣሥ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የዩነቨርሲቲው መምህራን ተማሪዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት የበየነ መረብ ውይይት ቢቋረጥም ቀን መታሰቡ እንደ ሀገር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ።
እለቱን ታስቦ መዋሉ አስፈላጊነቱም በኢትዮጵያም ብዝኃነትን የሚያከብር፣ አብሮነትን ገንዘብ ያደረገ፣ ኃላፊነት የሚሰማዉ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረዉን ጥረት ለማገዝ፣ ማኅበራዊ ዕሴቶቻችንን ለማሳደግና ለለውጥ ዝግጁ ዜጋና ኅብረተሰብ ለመፍጠር ተቻችሎ መኖር አንዱ ለአንዱ አስፈላጊዉ አንደኾነ ለማስረጽና ግንዛቤ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው የየኒቨረሲቲው የአካዳሚክ ምር/ቴክ/ሽግግርና ማ/አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ስለሽ አቢ ተናግረዋል ፡፡
በበየነ መረብ ሊደረግ የነበረው ወይይት ቢቋረጥም ቀኑ ታስቦ መዋሉ ለሀገር ግንባታ ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ መሆኑን ያነጋገርናቸው ውይይቱን ለመሳተፍ የመጡ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ፡፡




