የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት አድስ የትምህርት አስተዳደር ስርዓት ሶፍትዌር አስተዋወቀ።
******************************************************
ጥር 1/2016 (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
<<Learning Management System (LMS) >>የተባለ የመማር ማስተማ ስራን በድጅታል ቴክኖሎጅ ለመደገፍ የሚያግዝ ፕላት ፎርም የቴክኖሎጂ ውጤት ስራ ላይ ለማዋል ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብርሀም በለጠ ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን በትውውቅ ፕሮግራሙ ላይ ገልፀዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻውል እንድህ አይነት ስራዎች በተነሳሽነት በመጀመሩ አበረታች መሆኑን ገልፀው መሰል የፈጠራ ስራችዎን የማስተዋወቅና በቀጣይነት እያሻሻሉ መሄድ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡