የወሎ አዋሲ በግ ዝርያ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ጋር ውይይት ተካሄደ ፡፡

*****************************************************

(ጥር /2016 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

በጊምባ ከተማ አስተዳደር የ025 ቀበሌ ቱሉ አባ ገዳ መንደር በክላስተር ተደራጅው የወሎ X አዋሲ በግ ዝርያ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች በማህበረሰብ አገልግሎት የበጎች የጉበት በሽታ መከላከያ መድሀኒት ስርጭት ወቅት በዝርያ ማሻሻሉ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱም የመኖ እና የውሀ እጥረት በአቅራቢያቸው ስላጋጠማቸው ከዝርያው የተሻለ ምርት ለማግኘት ችግር እንደፈጠረባቸው አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ካሳ ሻውል (ዶ/ር ) በቦታው ተገኝተው አርሶ አደሮቹን ያወያዩ ሲሆን የተጀመረው ዝርያ የማሻሻል ሰራው ጅማሮው ጥሩ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረው ያገጠመውን የመኖ እጥረትና የውሀ ችግር በቀጣይ እየተጠና በሂደት የሚፈታ እንደሆነ ለአርሶ አደሮቹ አመላክተዋል፡፡ለተደራጁት በእለቱም ለአርሶ አደሮቹ የበጎች ጉበት በሽታ መከላከያ መዲሀበኒት ስርጭት ተካሂዷል፡፡