ለ1ኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች የህይወት ክህሎትእና የስርዓተ ጾታ ስልጠና ተሰጠ ፡

(የካቲት 2016 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙንት)

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ በ2016 ዓ.ም አድስ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመድበው ለገቡ የ1ኛ አመት መደበኛ ተማሪወች የህይወት ክህሎትና የስርዓተ ጾታ ስልጠና ፤ ወጣትነትና የህይወት ክህሎት፣ ራስን የመምራት ክህሎት ና የስነ-ተዋልዶ ጤና በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ለ2 ተከታታይ ቀናት ተሰጥቷል ፡፡

በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሰብለወርቅ አበበ እንደተናገሩት ስልጠናው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው ተማሪወች ለአካባቢው አድስ ከመሆናቸው አንፃር ችግሮች ቢገጥሟቸው እንደት ማለፍ እንዳለባቸው፤ ከተለያየ አካባቢ ከመጡ ተማሪዎች ጋር እንደት ተግባብተው መኖር እንዳለባቸው፤ እንድሁም ይህ ስልጠና ከዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው አልፎ ለቀጣይ የህይወት ጉዟቸው የሚረዳ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ተማሪወች በበኩላቸው እንደተናገሩት ስልጠናው በጣም አስፈላጊ እና ለህይወታቸው ጠቃሚ ትምህርት ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለለውጥ እንተጋለ !!Striving for change!!