በስነ- ምድር ትምህርት ክፍል የሴሚናር ጽብረቃ ተካሄደ።

Research News University News

በስነ- ምድር ትምህርት ክፍል የሴሚናር ጽብረቃ ተካሄደ።

(የካቲት 2016 የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የስነ- ምድር ትምህርት ክፍል Hydro geo chemical analysis and environmental isotopic signature of ground water upper blue Nile area >>በሚል ርዕስ ሴሚናር (ጥናታዊ ፅሁፍ ) መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው አበባው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡

በሴሚናሩ ወቅት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ አስማማው ምኒልህ እንድህ አይነት ፕሮግራሞች መኖራቸው አዳድስ ሀሳቦች የሚፈልቁበት ፤ እርስ በእርስ የምንማማርባቸው እንድሁም፤ተማሪዎቻችንም ተሞክሮ የሚቀስሙበት ከመሆኑም ባሻገር የአካዳሚክ ሰራተኛውን የምርምር ስራ የሚያጠናክር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

ተሳታፊዎችም የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን በከርሰ ምድር ላይ ሚደረግ የማዕዲናት ጥናትና ምርምር የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከል አንዱ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ለማድረግ መሰል ስራዎችን በየሳምንቱ እንደሚቀርቡና መምህራን መሳተፍ እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል ፡፡

ለለውጥ እንተጋለን ! striving for change!

ለለውጥ እንተጋለን!Striving for change!

ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *