በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መከነሰላም ካምፓስ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በስነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
(የካቲት /2016 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ በመከነሰላም ግቢ በስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈፃሚ አዘጋጅነት ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በስነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ዙሪያ በመካነሰላም ካምፓስ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውም የስነ-ምግባር ግድፈት ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር ከፍች መሆኑን በመተንተንና በማስረዳት እንደት የሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች እንደሚቀለበሱ ግንዛቤ ማስጨበጥ የስልጠናው የትኩረት አቅጣጫ ነው።
በመሆኑም የስነ ምግባር መኮስመን የስብእና መጓደል መሆኑን በማብራራት ሙስናና ብልሹ አሰራር እጅግ እየተስፋፋ ሀገርንና ትውልድን እየቀበረና በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ የአስተሳሰብ ውድቀት ውስጥ እጨመረ ዜጎች በሰላም እጦትና በኑሮ መቃወስ እየፈጠረ መሆኑ ቀላል የማይባል ጉዳት ማድረሱን የዩንቨርስቲው የስነዜጋና ስነ ምግባር መ/ር እያሱ ዘለቀ በስልጠናው ወቅት ጠቁመዋል።መ/ር መሃመድ ኢብራሂም በበኩላቸው በስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑንና የጥናቱም ውጤት ሲጠናቀቅ ያመጣውን ለውጥ ይፋ እንደሚያደርጉ አክለው ገልፀዋል።
ሰልጣኞችም በበኩላቸው ብልሹ አሰራርና ሙስና ከራስ ጀምሮ በመጠየፍና በማስተማር ሀላፊነት በመውሰድ መከላከል እንደሚቻልና ለውጥ እንደሚመጣ ከስልጠናው ያገኙት ጭብጥ መሆኑን በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።
ለለውጥ እንተጋለን ! striving for change!
ለለውጥ እንተጋለን!Striving for change!
ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!