የመቅደላ እምባ ዪኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎት በጎችና ፍየሎችን ክትባት መስጠቱን የአካዳሚክ ም/ቴ/ሽግግርእና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

University News

የመቅደላ እምባ ዪኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎት ከ 80 ሽህ በላይ በጎችና ፍየሎች ን የ<< ovine Pastuerellosis>>ክትባት መስጠቱን የአካዳሚክ ም/ቴ/ሽግግርእና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኙ 9 ወረዳዎች የምርምር ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራ በመስራት የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል፤ ፡፡ በዚሁ መሰረት በ2016 የበጀት አመት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምርምር፣ ቴክኖሎጅ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በተመራማሪ መምህራን የተዘጋጀ ‹‹Provision of mass vaccination toovine in Tenta Districts of south wollo zone , Ethiopia ›› በተባለ ፕሮጀክት በተንታ ና በለጋምቦ ወረዳ ዎች ለ80 ሽህ በጎችና ፍየሎች የ‹‹ovine Pastuerellosis ››ክትባት በዩኒቨርሲቲው መምህራንና በወረዳዎቹ የዘርፉ ባለሙያዎች ቅንጅት እንድሰጥ ተደርጓል ፡፡

በለጋምቦ ወረዳ 026 ቀበሌ ተገኝተው ክትባቱን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር ቴ/ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ረዳት አስተዳዳሪና ተመራማሪ ዋለ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ የሚገኙ የተንታና ለጋምቦ ወረዳዎች ከፍተኛ የበጎችና ፍየሎች ክምችት ባለባቸው ቀበሌዎች በመለየት የሚካሄድ እንደሆነ ገልጸው ovine Pastuerellosis ክትባት የመስጠት ብቻ ሳይሆን የህክምና መስጫ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ጭምር የተደረገ ድጋፍ ሲሆን በዋጋ ሲገመት ከ385 ሽህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የክትባቱ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት የተከሰተውን የበጎች በሽታ ለመከላከል ዩኒቨርሲቲው ቅዲሚያ ሰጥቶ ላደረገላቸው ጉልህ አስተዋፆ ከፍ ያለ ምስጋና እንዳላቸው ገልጸዋል ፡፡

ለለውጥ እንተጋለን!Striving for change!

ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *