የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የቤተሰብ ምስረታ ፕሮግራም አካሄደ፤
(7/08/2016ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአካባቢውን ማህበረሰብ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በማስተሳሰር የተሰጠውን ተግባር ለመወጣት ለተማሪዎቹ ምቹና ሰላማዊ መማር ማስተማር እንድኖር እና ተማሪዎች ከየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ የመጡ በመሆኑ ባይታዋርነት ሳይሰማቸው የመጡበትን አላማ፣ እንዳሳኩ ልዩ የሆነ የቤተሰብ ምስረታ አካሂዷል ፡፡
በእለቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ጥ/ም/ቴ/ሽ እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ስለሽ አቢ ( ዶ/ር) እንደተናገሩት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ምንም አይነት ከቤተሰብ የመራቅ ስሜት ሳይሰማችሁ እንደ እናት እና አባት ጠብቀውና ተንከባክበው ፤እንደ ልጆቻቸው ተቀብለው ሊጠብቋችሁ የሚችሉ ና ፈቃደኛ የሆኑ ቤተሰቦችን በመመስረት በግቢ ቆያታችሁ ያለ ምንም ስጋት ትምህረታችሁን እንድትከታተሉ የሚያስችል ተግባር በመሆኑ እድልን በማገኘታችሁ ደስ ሊላችሁ ይገባል ብለዋል ፡፡
የጊንባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እያሱ አባይ በቤተሰብ ምስረታው ላይ ተግኝተው እንደተናገሩት‹‹ የወሎ ህዝብ ሰው ከየት መጣህ ተብሎ የማይጠየቅበት ደግና አቃፊ ማህበረሰብ ያለበት በመሆኑ ተማሪዎች ከተለያየ አካባቢ እንደመምጣታቸው ደህንነታቸውየተጠበቀና ቤተሰባዊ ስሜት እንድሰማቸው ፤የአካባቢው ማህበረሰብ የአቃፊነት ባህሉን በተረከባቸው ልጆች አባታዊና እናታዊ ስሜት ባሳየ መልኩ ግንኙነት እንደፈጥሩ ፤ታስቦ የተካሄደ በመሆኑ ቀጣይነት ያለው ቤተሰባዊ ግንኙነት እንድኖር ሲሉ ተናግረዋል ፡፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ስውአገኝ አስራት (ዶ/ር) በፕሮግራሙ ማጠቃለያ እንዳሳሰቡት በዚህ ተግባር 3000 የሚደርሱ ተማሪዎችን 350 ለሚሆኑ ወላጆች አገናኝተናል ብለዋል ይህም የሆነው ከወላጆች ከልብ የመነጨ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ተግባሩን ተዘጋጅቶ ወላጆች ልጆቻቸውን በይፋ ተረክበዋል ብለዋል፡፡አክለውም ተማሪዎች የትኛውም ችግር ቢገጥማቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተወያይተው እንደሚፈቱ መልካማ አጋጣሚ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ለለውጥ እንተጋለን!Striving for change!
ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!