የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከአቀስታ ከተማ አስተዳደር ስራና ስልጠና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ያስገነባውን የዶሮ እርባታ ማዕከል ለተደራጁ ወጣቶች አስረከበ፡፡

Research News University News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከአቀስታ ከተማ አስተዳደር ስራና ስልጠና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ያስገነባውን የዶሮ እርባታ ማዕከል ለተደራጁ ወጣቶች አስረከበ፡፡

(ሚያዚያ/2016 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት)

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ <<Creating Job opportunity for unemployed youth on small scale Chiken production in Legambo and Tenta District of South Wollo Zone Ethiopia>> በሚል ርዕስ በተሰራ ፕሮጀክት 243 የአምስት ወር እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በ66 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ስታንዳርዱን የጠበቀ የዶሮ ቤትና የምግብ፣የህክምናና ሌሎች ግብአቶችን ያሟላ ግምቱ ከ800ሺ ብር በላይ የሆነ በአቀስታ ከተማ አስተዳደር ስር ለተደራጁ 5 ወጣቶች የሀብትና ንብረት ሚያዚያ18/2016 ዓ.ም ርክክብ ፈጽሟል፡፡

በርክክቡ ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ምርምር፣ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ስለሺ አቢ እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ ከጎን ሆኖ የቦታና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ፈጥኖ በመመለስ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበው ፕሮጀክቱ እውን ሆኖ ማየታቸውም እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል፡፡

የአቀስታ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ ብርሃን ሺመልስ በበኩላቸው እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የወጣቶችን ችግር በመገንዘብ ስራ ከመፍጠሩ ባሻገር ለሌሎች ወጣቶች አርአያ እንድሆኑ ላደረገው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው በቀጣይነትም ዩኒቨርሲቲው በከተማ አስተዳደሩ ዙሪያ ሊሰራባቸው የሚችሉ ፀጋዎችን በማልማት አብሯቸው እንድሰራ ጠይቀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ የሆኑት መምህርና ተመራማሪ ተራማጅ አበበ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ሲታሰብ ለሁለት ዋና ዋና አላማ ሲሆን 1ኛው ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እና 2ኛው በአካባቢው ያለ ማህበረሰብ ከዚህ ፐሮጀክት ሞደል በማድረግ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ እንድያስፋፋ ማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡አክለውም ፕሮጀክቱ ተሳክቶ ማየታቸው እንዳደሰታቸው እና አብረዋቸው የፕሮጀክቱ አባል ሆነው የሰሩትን ባልደረቦቻቸውን አመስግነዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩም መምህርና ተመራማሪ ተራማጅ አበበ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ እውን እንድሆን ላደረጉት አሰተዋጽኦ የአውቅና ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *