ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ትምህርት ክፍል የሴሚናር ጽብረቃ አካሄደ
(ግንቦት 21/2016 የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት) የግብርና ና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የተፈጥሮ ሃብት አያያዝ ትምህርት ክፍል ‹‹Future Hydrology of the Upper Blue Nile Basin and its Impact on Grand Ethiopian Renaissance Dam water Resources system>> በሚል ርዕስ የኮሌጁ መምህራንና የትምህርት ክፍሉ ተመራቂ ተማሪዎች በተገኙበት በመምህርና ተመራማሪ ካስየ ሽቱ ጥናታዊ ጽሁፍ( ሲሜናር ጽብረቃ) ቀረቦ ውይይት ተካሂዶበታል ፡፡
በሴሚናሩ ወቅት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን ተባባሪ ፕሮፌሰር አማረ ግርማ ለተሳታፊዎችና ሲሚናር አቅራቢ ምስጋናቸውን ገልፀው‹‹ የሲሜናር ፕሮግራም መዘጋጀቱ አዳድስ ሃሳቦችን ከማግኘት ባሻገር ለመምህራን ተነሳሽነትን በመፍጠር አዳድስ የምርምር ግኝቶችን ለማግኘት ይረዳል›› ብለዋል፡፡አክለውም ‹‹የውሃ ሀብት አጠቃቀምና የአካባቢ ጥበቃ ላይ ጥናት ማድረግ ደግሞ እንደ ሀገር ትልቅ ጉዳይ በመሆኑ ይህን ሴሚናር ወሳኝ ያደርገዋል ብለዋል ፡:
በቀጣይም ሁሉንም አሳታፊ የሆኑ ና ጠቃሚ ስራዎች በተሻለ መልኩ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡