Research News University News

በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል የሴሚናር ጽብረቃ አካሄደ፡

( ሰኔ 2016 ዓም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኑነት)

<<A survey on assessment of performing physical activity habit of Mekdla amba university›› እና ‹‹Medication we all need pilis to every one of us>>በሚሉ ሁለት ርዕሶች ላይ በመምህር ሰለሞን ሃብታሙ እና በመምህር ሰለሞን አሳየ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡በእለቱም የ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ሴሚናሩን በንግግራቸው የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አስማማው ምኒልህ እንደተናገሩት በዚህ አመት ብዙ ሴሚናሮች እየቀረቡ እና እየተማማርንባቸው ነው ብለው ፤ በስፖርት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀው የዛሬው ሴሚናር ደግሞ ሰፖርት ለጤናችን አስፈላጊ በመሆኑ የአካል ባቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ባህላችን እንዲናደርግ መነቃቃትን የሚፈጥር ይሆናል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ አለም ላይ እየተከሰቱ ያሉትን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መደበኛ የሆነ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ልምድ በማድረግ መቀነስ እንደሚቻል ግንዛቤ ተይዟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *