በምርምር ትልሞች ላይ የውስጥ ግምገማ ተደረገ

Research News University News

በምርምር ትልሞች ላይ የውስጥ ግምገማ ተደረገ

ሰኔ 24/20 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ምርምር፣ህትመትና ስነምግባር ስርፀት ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም የስራ ዘመን ወደ ተግባር የሚገቡ የምርምር ትልሞች ተዘጋጅተው ወደ ስራ ክፍሉ እንዲቀርቡ ለተመራማሪዎች ባቀረበው ጥሪ መሰረት 112 የምርምር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ትልሞች ቀርበዋል፡፡ የምርምር፣ህትመትና ስነምግባር ስርፀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አገኝ ሽበሺ (ዶ/ር) የውስጥ ግምገማ መድረኩን የከፈቱ ሲሆን የአመቱ ስራ በሚጠናቀቅበትና በርካታ የስራ ጫና ባለበት ወቅት ተመራማሪዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው አመስግነው ግምገማው በጥራት እንዲከናወንና የተጣሩት የጥናት ትልሞች ደግሞ ወደ ቀጣዩ ሂደት እንዲቀርቡ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *