የ2017 ዓ.ም የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የጥናት ትልሞች ላይ ግምገማ ተካሄደ፡፡
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ግቢ የ2017 ዓ.ም የምርምርና ማህበረሰብ አግልግሎት በማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ ኮሌጅ፣ በንግድና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን ባቀረቧቸው 10 ፕሮፖዛሎች ላይ በቀን 26/10/2016ዓ.ም ግምገማ አካሂዷል፡፡
በሁለት መድረክ በተመራው የፕሮፖዛሎች ግምገማ ላይ የተገኙት የግቢው ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ አብዱሮህማን አወል በመክፈቻ ንግግራቸው በ2017 ዓ.ም ከምንሰራቸው ቁልፍ ስራዎች አንዱ በሆነው በምርምርና ማህበረሰብ አግልግሎት ዙሪያ ፕሮፖዛሎች ቀርበው ግምገማ ሲደርግባቸው ክፍተቶቻቸውን በመሙላት በማህበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ከወድሁ ማሳደግ ስለሆነ ልዩ ትኩረት ሰጥተን ልናያቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የመካነ ሰላም ግቢ ምርምርና ሀገር በቀል ዕውቀት አስተባባሪ ቀሲስ አያሌው አራጌ በግምገማ ወቅት እንደተናገሩት በማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስ ኮሌጅ መምህራን የቀረቡት ፕሮፖዛሎች ከግብረ ገብነትና ስነምግባር አኳያ ስነ-ቃል ያለው ማሳያ፤ የመምህራን የግምገማ ልምድ፤ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ላይ የአካዳሚክ ዘርፉ ዕይታ፤ ለማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅና ለጋራ ኮርስ አስተማሪዎች የሚሰጠው የSPSS ስልጠና፤ ንባብና የንባብ ባህል እንድሁም የእስልምናና የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ታሪካዊ የግንኙነት ጥናት (1855-2000ዓ.ም) የሚሉ ይዘቶችን ያነሱ ናቸው፡፡
በንግድና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን በኩል ቀርበው የተገመገሙት ይዘቶች ደግሞ የገንዘብ አቅምን የሚወስኑ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ጉዳይ፤ የክዋኔ ኦድት ውጤታማነትና በባንክ የወረፋ ንድፈ ሃሳብ አተገባበር የሚሉ ናቸው፡፡ ሁሉም ተተኳሪነታቸውን ያደረጉት በደቡብ ወሎ ዞን በተመረጡ የምእራብ ወረዳዎች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አስተባባሪው አክለውም ይህ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮፖዛል ግምገማ ሲደረግ ታሳቢነቱ በዋናነት ለበጀት ካውንስሉ የተሻሉና ጥራት ያላቸው የምርምር ፕሮፖዛሎችን አቅርቦ ለማጽደቅና ወደ ስራ ለማስገባት ያመች ዘንድ ስለሆነ ጥቅሙ ትልቅ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ለወቅታዊ አና ታማኝ መረጃወች
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!