መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

University News

(የካቲት 8/2017 የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለ5ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቅድመ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 998 ተማሪዎችን በቱሉ አውሊያ ዋናው ግቢ ዛሬ የካቲት 08/2017 ዓ.ም አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳ ሻውል ለዕለቱ ተመራቂ ተማሪዎች፣ ለተመራቂ ቤተሰቦችና በምረቃው ለተገኙ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አክለዉም ለተማሪዎች በሚያጋጥማችሁ ችግሮች ሳትደናቀፉ በብስለት ተቋቁማችሁ ለዚህ ቀን ስለደረሳችሁ እንኳ ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን ለባለድርሻ አካላትም የደስታና የችግሮቻችን ተካፋይ በመሆን የዛሬውን ውጤት በማየታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር ከፍያለው አለማየሁ በበኩላቸው የተለያዩ ድርብርብ ፈተናዎችን አልፋችሁ ለዚህ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ተመራቂዎች አሁን እናንተ በምትመረቁበት ሰዓት ሃገራችን ሰላምን፣ ፍቅርና መተባበርን በምትሻበት ጊዜ በመሆኑ እናንተም የድርሻችሁን እንድትወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ አማካሪና ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሰይድ ሙሃመድ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በሃገር ደረጃ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና 87%

በማሳለፍ ለምረቃ በማብቃቱ የተሻለ ጥረት ማድረጉን ያሳያል ብለዋል።

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር ጥጋቡ በቀለ በ5ኛው ዙር ተማሪዎች፣ በዋናው ቱሉ አውሊያ ግቢ መደበኛ:በክረምት እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር በጥቅሉ በሁለቱም ግቢ በመጀመሪያ ድግሪ 998 ተማሪዎች እንዲመረቁ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የካቲት 07/2017 ዓ.ም መርምሮ ባጸደቀው መሠረት መመረቃቸውን አብስረው ለተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡

በመጨረሻም ከአጠቃላይ ተመራቂዎች በውጤታቸው ብልጫ ላመጡ ተማሪዎች ልዩ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

ለወቅታዊ አና ታማኝ መረዎጃች

website – https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA

ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *