በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትናችሁ በ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለዚህ ታላቅ የትምህርት ስኬት በሰላም አደረሳችሁ!!

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የወደፊት ህልማችሁን የምትቀርጹበት፣ እውቀታችሁን የምታሰፉበት፣ ማህበራዊ ህይወታችሁን የምታቃኑበትና የስኬት ማማ ላይ የምትወጡበት የትምህርት ማዕከላችሁ አድርጋችሁ እንደምትመርጡት ሙሉ እምነት አለው፡፡

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲን የመጀመሪያ ምርጫችሁ አድርጋችሁ የምትመርጡትም፡-

  • በቂ የንድፈ-ሐሳብና የተግባር ልምድ የሚያስጨብጥ ዘመናዊ የመማር-ማስተማር ሂደትን የሚከተል በመሆኑ፣
  • ለምርምርና ለግል እድገት ምቹ የሆኑ መሰረተ-ልማቶች ያሉትና የተረጋጋ ግቢ በመሆኑ፣
  • ወደ ግቢ ከገባችሁበት ቀን ጀምሮ እስከምትመረቁበት እለት ድረስ ከጎናችሁ የማይለይ ቤተሰባዊ ድጋፍ የሚያደርግ በመሆኑ ነው።

የነገዋን ብሩህ ተስፋችሁን ዛሬ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ጀምሩ! ምርጫችሁን መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲን ስለምታደርጉ እናመሰግናለን!!

እምቅ አቅምን በመጠቀም ነገን እንገነባለን!!

Unlock Potential, Shape the Future!

Leave a Comment